ማንቼስተር ሲቲ አርሰናልን በማሸነፍ ነጥቡን አጠበበ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ33ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ተጠባቂ ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ አርሰናልን 2 ለ 1 አሸንፏል።
በሜዳው ኢትሃድ ምሽት 12 ሰዓት ከ30 ላይ የሊጉን መሪ አርሰናልን ያስተናገደው ማንቼስተር ሲቲ ቼሪኪ እና ሃላንድ ባስቆጠሯቸው ግቦች ነጥቡን ወደ ሶስት ለማጥበብ ያስቻለውን ድል አስመዝግቧል።
የአርሰናልን ብቸኛ ግብ ካይ ሀቨርት ከመረብ ጋር አገናኝቷል።