Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ አፍሪካ በሚሊየን የሚቆጠሩ ስደተኞች ለረሀብና ለተመጣጠነ ምግብ እጥረትሊጋለጡ ይችላሉ-ተመድ

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 21 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በምስራቅ አፍሪካ በሚሊየን የሚቆጠሩ ስደተኞች ለከባድ ረሀብ እና ለተመጣጠነ ምግብ እጥረት ሊጋለጡ እንደሚችሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ።

የዓለም የምግብ ድርጅት እንደገለጸው ÷ በድርጅቱ በሚሰጡት የምግብ ድጋፍ ላይ ጥገኛ የሆኑ በሚሊየን የሚቆጠሩ ስደተኞች ለባድ ረሀብ እና የተመጣጠነ ምግብ እጦትይጋለጣሉ ብሏል።

ለዚህም ምክንያቱ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተፅእኖ ከለጋሽ አካላት አስፈላጊውን የገንዘብ ድጋፍ ማግኘት አለመቻሉ መሆኑን አስታውቋል።

ስለሆነም ድርጅቱ በኢትዮጵያ ፣ በኡጋንዳ ፣ በኬንያ ፣ በደቡብ ሱዳን እና በጅቡቲ  ስደተኞች ካምፕ ውስጥ ለሚገኙ ከ 2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ለሚበልጡ ስደተኞች  የሚያደርገውን የምግብ እና የገንዘብ  ድጋፉ 30% ያህል ቅናሽ ማድረጉን  ገልጿል።

ከዚያም ባለፈ ስደተኞቹ ካምፑ ውስጥ ባለው በቂ ያልሆነ መጠለያ፣ደካማ የጤና አገልግሎት ስርዓት እና በንጹህ የመጠጥ ውሃ ችግር ምክንያት ለኮቪድ -19 መስፋፋት ተጋላጭ ናቸው ብሏል።

ምንጭ፡-ቢቢሲ

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.