ማንቼስተር ዩናይትድ ከብሬንትፎርድ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ34ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ዩናይትድ በሜዳው ኦልድትራፎርድ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ብሬንትፎርድን ያስተናግዳል፡፡
የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ ቦታን ለማግኘት እየተፋለመ የሚገኘው ማንቼስተር ዩናይትድ በሊጉ ተከታታይ 2ኛ ድሉን ለማሳካት ወደ ሜዳ የሚገባ ይሆናል፡፡
በሊጉ ያለፉትን አምስት ተከታታይ ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ያጠናቀቀው ብሬንትፎርድ በበኩሉ ወደ አሸናፊነት ለመምጣት ይፋለማል፡፡
ሁለቱ ቡድኖች እርስበርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ሁለቱም በተመሳሳይ ሁለት ጊዜ ድል ሲያደርጉ በቀሪው አንድ ጨዋታ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል፡፡
ሊጉን አርሰናል በ73 ነጥብ ሲመራው ማንቼስተር ሲቲ በ70፣ ማንቼስተር ዩናይትድ በ58 ነጥብ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡