Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በሚገጥሟት ተግዳሮቶች ሳትገደብ ከሚገመተው በላይ በከፍተኛ ፍጥነት እየተገነባች ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በሚገጥሟት ተግዳሮቶች ሳትገደብ ከሚገመተው በላይ በከፍተኛ ፍጥነት እየተገነባች ነው አሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የማህበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ” በሚል መሪ ሀሳብ በማህበራዊ ዘርፍ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ዐበይት ውጤቶች በቀረቡበት የምክክር መድረክ ላይ ተገኝተው ሃሳባቸውን አጋርተዋል።

‎የማህበራዊ ዘርፍ ግንባታ እንደ ሌሎች መሠረተ ልማቶች ውጤቱ ወዲያው የሚታይና የሚጨበጥ ባይሆንም ለሀገር ዘላቂና ወሳኝ መሰረት የሚጥል ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ በሚገጥሟት ተግዳሮቶች ሳትገደብ ከሚገመተው በላይ በከፍተኛ ፍጥነት እየተገነባች ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የዐቅም ውስንነቶች ቢኖሩም ለማሻሻል ያልተሞከረ የማህበራዊ ዘርፍ እንደሌለ ገልጸዋል።

‎በዘርፎች የታለመው ሁሉ በተግባር እንዲተረጎምና ተገቢውን ዓላማቸውን እንዲያሳኩ ብዙ ሥራ ይጠበቅብናል ነው ያሉት፡፡

አንድ እጅ ብቻውን ማጨብጨብ አንደማይችል ሁሉ መንግሥት የሚጀምራቸውን ሥራዎች ሌላው የማህበረሰብ ክፍል እንደ አንድ ባለ ድርሻ ኃላፊነት ወስዶ በጋራ መቆም እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.