ኤቨርተን ከማንቼስተር ሲቲ…
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ35ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ሲቲ ከሜዳው ውጭ ኤቨርተንን ይገጥማል፡፡
የዛሬ ምሽቱን ጨምሮ ሁለት ቀሪ ጨዋታዎች በእጁ የሚገኘው ማንቼስተር ሲቲ ከአርሰናል ያለውን የስድስት ነጥብ ልዩነት ለማጥበብ ወደ ሜዳ ይገባል፡፡
በቀጣይ የውድድር አመት የአውሮፓ መድረክ ተሳትፎን ለማግኘት እየተፋለመ የሚገኘው ኤቨርተን በበኩሉ ለማንቼስተር ሲቲ ቀላል ተጋጣሚ እንደማይሆን ይጠበቃል፡፡
ጨዋታው ምሽት 4 ሰዓት ላይ በአዲሱ ሂል ዲኪንሰን ስታዲየም ይደረጋል፡፡
በሌላ የሊጉ የጨዋታ መርሐ ግብር አሰልጣኙን በማሰናበት የኤፍ ኤ ዋንጫ የፍጻሜ ተፋላሚ መሆኑን ያረጋገጠው ቼልሲ በስታምፎርድ ብሪጅ ኖቲንግሃም ፎረስትን ያስተናግዳል፡፡
በ48 ነጥብ 9ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የአውሮፓ መድረክ ቦታን ለማግኘት የሚጫወት ሲሆን፥ ጨዋታው ቀን 11 ሰዓት ላይ ይጀምራል፡፡