ኢዜአ መንግሥት ባደረገው ሪፎርም ዳግም ተወልዷል ማለት ይቻላል – አቶ ሰይፈ ደርቤ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከምስረታው ባልተናነሰ የለውጡ መንግሥት በዘርፉና በተቋሙ ባደረገው ሪፎርም ምክንያት ዳግም ተወልዷል ማለት ይቻላል አሉ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ ሰይፈ ደርቤ።
አቶ ሰይፈ ደርቤ ”የሚዲያ እመርታ ለትርክት ግንባታ” በተሰኘው ሀገራዊ የምክክር መድረክ ላይ እንደገለጹት÷ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከምስረታው ባልተናነሰ የለውጡ መንግሥት በዘርፉና በተቋሙ ባደረገው ሪፎርም ምክንያት ዳግም ተወልዷል ማለት ይቻላል።
የተከናወነው የእሳቤ፣ የህግና አደረጃጀት እንዲሁም የአሰራር ሪፎርም የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን በአፍሪካ አስተማማኝና ተጽዕኖ ፈጣሪ የዜና ምንጭ በመሆን ብሔራዊ ጥቅምን ማስጠበቅና ብሄራዊ መግባባት መፍጠር የሚያስችል አቅም እንዲላበስ አስችሎታልም ነው ያሉት።
ተቋሙ ተደራሽነቱን በማስፋት፣ በቴክኖሎጂ ተደራጅቶ፣ ከኢትዮጵያ ተሻግሮ የአፍሪካ ድምጽ በመሆን የወል ትርክትን እየገነባ ይገኛል ማለታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል።