ለውጡ በእሳቤ፣ ህግና አሰራር ላይ ትኩረት በማድረግ ተቋማዊ ብቃትን አጎልብቷል – አቶ ብሩክ ከበደ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሀገራዊ ለውጡ ትኩረቱን በዋነኛነት በእሳቤ፣ በህግና አሰራር ላይ በማድረግ በሚዲያው ዘርፍ ተቋማዊ ብቃትና ሥነ ምግባርን አጎልብቷል አሉ የናሽናል ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ስራ አስኪያጅ ብሩክ ከበደ፡፡
አቶ ብሩክ ከበደ ”የሚዲያ እመርታ ለትርክት ግንባታ” በተሰኘው ሀገራዊ የምክክር መድረክ ላይ በዘርፉ በተለይም በኤንቢሲ የተመዘገቡ የለውጡን ስኬቶች አንስተዋል።
ለውጡ ትኩረቱን በዋነኛነት በእሳቤ፣ በህግና አሰራር ላይ በማድረግ ተቋማዊ ብቃትና ሥነ ምግባር ማጎልበቱን አስረድተዋል፡፡
ኤንቢሲ ኢትዮጵያ ለዲጂታላይዜሽን ቅድሚያ በመስጠት የመረጃ ንፉግነትን ባህል በመቀየርና የወል ትርክት በመገንባት ተቀዳሚ የሚዲያ ተቋም መሆን ችሏል ማለታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል።