Fana: At a Speed of Life!

ለሀላባ ከተማ ተጫዋቾች ሽልማት ተበረከተ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀላባ ከተማ አስተዳደር የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ አሸናፊ ለሆነው የሀላባ ከተማ ተጫዋቾች የገንዘብ እና የቤት መስሪያ ቦታ ሽልማት አበርክቷል፡፡

የ2018 የኢትዮጵያ ከፍተኛ አጠቃላይ የዋንጫ አሸናፊ የሆነው ሀላባ ከተማ ክለብ ወደ ሀላባ ከተማ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

ክለቡ ወደ 2019 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እንዲቀላቀል ላደረጉ የአሰልጣኝ ቡድን አባላት እና ተጫዋቾች የቤት መስሪያ ቦታ እና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ከዚህ በፊት ክለቡን ለመደገፍ ሲጓዙ ሕይወታቸውን ላጡ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ደጋፊዎች እና ቤተሰቦቻቸው የማስታወሻ እና የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል።

በሽልማት ሥነ ሥርዓቱ የሀላባ ቁሊቶ ከተማ ከንቲባ፣ የክለቡ ፕሬዚዳንት ገመዳ መሃመድ፣ የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሙዲን ሁሴን እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና የክለቡ ደጋፊዎች ተገኝተዋል።

ሀላባ ከተማ ጋሞ ጨንቻን በመለያ ምቶች 4 ለ 3 በማሸነፍ የ2018 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ አጠቃላይ አሸናፊ መሆኑ ይታወሳል።

በእንዳልካቸው ወዳጄ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.