ማንቼስተር ዩናይትድ ኖቲንግሃም ፎረስትን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ37ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ዩናይትድ ኖቲንግሃም ፎረስትን 3 ለ 2 አሸንፏል።
ቀን 8:30 ላይ በኦልድ ትራፎርድ በተደረገው ጨዋታ የዩናይትድን ግቦች ሉክ ሻው፣ ማቲዎስ ኩንሃ እና ብራያን ምቤሞ አስቆጥረዋል።
የኖቲንግሃም ፎረስትን ከመሸነፍ ያልታደጋቸውን ግቦች ደግሞ ሞራቶ እና ጊብስ ዋይት ከመረብ አሳርፈዋል።
የሊጉ መርሐ ግብር ቀጥሎ ሲካሄድ አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ ብሬንትፎርድ ከክሪስታል ፓላስ፣ ሊድስ ዩናይትድ ከብራይተን፣ ወልቭስ ከፉልሃም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
እንዲሁም ምሽት 1፡30 ላይ ላለመውረድ እየተፋለመ የሚገኘው ዌስትሃም ኒውካስልን ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ይገጥማል።