ኒኮ ኦራይሊ የፕሪሚየር ሊጉ ምርጥ ወጣት ተጫዋች ሽልማትን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) እንግሊዛዊው የማንቼስተር ሲቲ ተጫዋች ኒኮ ኦራይሊ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ምርጥ ወጣት ተጫዋች ሽልማትን አሸንፏል፡፡
ከክለቡ አካዳሚ የተገኘው የ21 ዓመቱ ተጫዋች ከደጋፊዎች በተሰበሰበ ድምፅ ነው የምርጥ ወጣት ተጫዋች ሽልማትን ማሸነፍ የቻለው፡፡
ኒኮ ከአርሰናል ጋር እልህ አስጨራሽ የዋንጫ ፉክክር ባደረገው የማንቼስተር ሲቲ ስብብስብ ውስጥ የግራ መስመር ክፍሉን በብቃት በመምራት ምርጥ የውድድር ዓመትን አሳልፏል፡፡
በፕሪሚየር ሊጉ ማንቼሰተር ሲቲ ካደረጋቸው 37 ጨዋታዎች በ34ቱ ተሰልፎ መጫዎት የቻለው ኒኮ ኦራይሊ አምስት ግቦችን ሲያስቆጥር ሶስት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል፡፡