Fana: At a Speed of Life!

ትራምፕ ከኢራን ጋር በሚደረገው ድርድር ተደራዳሪ ቡድናቸው እንዳይቸኩል አሳሰቡ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር በሚደረገው ድርድር ተደራዳሪ ቡድናቸው በችኮላ እንዳይስማማ አስጠነቀቁ።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከኢራን ጋር እየተደረገ የሚገኘው ድርድር በተደራጀ ሁኔታ እና መፍትሔ በሚያመጣ መልኩ እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል።

ከኢራን ጋር ያለውን ጦርነት ማስቆምና የሆርሙዝ ሰርጥን ዳግም ማስከፈትን ጨምሮ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ድርድር መደረጉን ነው የገለጹት።

ይሁን እንጂ አሁን ጊዜው ለእኛ ነው፤ ስለዚህ መቸኮል አያስፈልግም በማለት የተደራዳሪ ቡድናቸውን አስጠንቅቀዋል።

ትራምፕ ከኢራን ጋር በስምምነቱ ዙሪያ ሰፊ ውይይት እንደተደረገ በመግለጽ ዝርዝሩ በቅርቡ ይፋ ይሆናል ማለታቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።

የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢስማኤል ባጋይ ከአሜሪካ ጋር እየተደረገ ያለው ንግግር መቀራረብ እየታየበት እንደሆነ ባለፈው ሳምንት መናገራቸው ይታወሳል።

በብርሃኑ አበራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.