Fana: At a Speed of Life!

ከተማ አስተዳደሩ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ወገኖችን በማቋቋም ወደ ስራ እያስገባ ይገኛል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለዜጎች ቅድሚያ በመስጠት ምንም ገቢ የሌላቸውንና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ወገኖችን ከመመገብ ባሻገር በማቋቋም ወደ ስራ እያስገባ ይገኛል አሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

ከንቲባዋ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ ዛሬ የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላት ተጠቃሚዎች ለነበሩ 400 ነዋሪዎቻችን መነሻ ካፒታልና የመስሪያ ቁሳቁስ አሟልተን ከተረጂነት ወደ የስራ እድል ተጠቃሚነት እንዲሸጋገሩ አድርገናል ብለዋል።

በዚሁም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለዜጎች ቅድሚያ በመስጠት ምንም ገቢ የሌላቸውንና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ወገኖችን ከመመገብ ባሻገር በማቋቋም ወደ ስራ እያስገባ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በመሆኑም በተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላት ዜጎችን ከመመገብ ባለፈ በተለያዩ ጊዜያት ከተረጅነት ወደ ስራ ፈጣሪነት መሸጋገር የሚችሉትን እየለየን የስራ እድል እንዲያገኙ ማድረግን አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል ነው ያሉት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.