Fana: At a Speed of Life!

ለሀገር ዕድገት ይበጃል የሚሉትን ለመምረጥ የተዘጋጁት የሶዶ ከተማ ነዋሪዎች…

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በመጪው ጠቅላላ ምርጫ ለሀገር ልማትና ዕድገት የሚበጀውን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል አሉ የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች፡፡
ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አስተያየታቸውን የሰጡ የከተማዋ ነዋሪዎች፥ ቤተሰቦቻቸውን ጭምር በማንቃት የድምጽ መስጫውን ዕለት በጉጉት እየጠበቁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
‌‎በህዝብ ምርጫ የሚመጣ መንግስት የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመፍታት እንደሚሰራ ገልጸው፥ የምርጫ ካርድ ከወሰድንበት ዕለት ጀምሮ ለሀገራችን ሁለንተናዊ ዕድገትን የሚያረጋግጥ ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል ነው ያሉት፡፡
ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስከብር ፓርቲን ለመምረጥ ያስችላል ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ፥ ሌሎችም ይህንን በመገንዘብ በምርጫው በንቃት እንዲሳተፉ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ካርድ ወስዶ ሳይመርጡ መቅረት የራስን መብት ለሌላው አሳልፎ መስጠት መሆኑን ገልጸው፥ ለሀገር ይበጃል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
‌‌‎በኢብራሂም ባዲ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.