ሪያል ማድሪድ የዓለማችን ውዱ ክለብ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21 ፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የስፔኑ ክለብ ሪያል ማድሪድ የዓለማችን ውዱ ክለብ መሆኑን ፎርብስ ይፋ አድርጓል፡፡
ፎርብስ መጽሔት በዛሬው ዕለት ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት÷ ሪያል ማድሪድ በ9 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ዋጋ የዓለማችን ውዱ ክለብ መሆን ችሏል፡፡
ሪያል ማድሪድ በውድድር ዓመቱ ስኬታማ ጊዜ ባያሳልፍም ለተከታታይ አምስተኛ ዓመት የዓለማችን ውዱ ክለብ በመሆን በቀዳሚነት ተቀምጧል፡፡
ሌላኛው የስፔን ክለብ ባርሴሎና በ7 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር 2ኛ ሲሆን÷ ማንቼስተር ዩናይትድ ደግሞ በ7 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ዋጋ 3ኛ ደረጃን ይዟል፡፡
በተጨማሪም ሊቨርፑል በ6 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር እና ፒኤስጂ በ5 ነጥብ 8 ቢሊየን ዶላር ዋጋ በተከታታይ 4ኛ እና 5ኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮኑ አርሰናል በ5 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ዋጋ 8ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
በመጨረሻ ሳምንት በሊጉ መቆየቱን ያረጋገጠው ቶተንሃም ሆትስፐር በበኩሉ በ3 ቢሊየን ዶላር ዋጋ 10ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
በወንድማገኝ ጸጋዬ