በድምጻችን በቀጣይ የሚወክለንን ፓርቲ ለመምረጥ ዝግጁ ነን – የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ነዋሪዎች
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሚበጃቸው ፓርቲ ድምጽ ለመስጠት ዝግጁ ነን አሉ።
ነዋሪዎቹ የምርጫ ካርድ ማውጣት በተጀመረበት የመጀመሪያ ቀናት ወደ ምርጫ ጣቢያዎቻቸው በማቅናት ካርድ መውሰዳቸውን ተናግረዋል።
የፖለቲካ ፓርቲዎችን የፖሊሲ አማራጭ በጥንቃቄ መከታተላቸውን ጠቅሰው ÷ ሕዝብን የሚጠቅም ፓርቲ በመለየት በምርጫው ዕለት ድምጻቸውን ለመስጠት በጉጉት እየጠበቁ መሆኑን ጠቁመዋል።
ምርጫው ዴሞክራሲያዊ፣ ሰላማዊና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱም አረጋግጠዋል።