Fana: At a Speed of Life!

በምርጫ ካርዳችን ለሀገርና ሕዝብ የሚበጀውን ፓርቲ ለመምረጥ በጉጉት እየጠበቅን ነው – የባቱና አሰላ ከተማ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ‎የሚወክለንን ፓርቲ ለመምረጥ የምርጫ ቀኑን በጉጉት እየጠበቅን ነው አሉ የባቱ እና አሰላ ከተማ ነዋሪዎች።

ነዋሪዎቹ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት÷ ‎7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሀገሪቱን ነፃነትና መልካም ስም ከማስፈን አንጻር ትልቅ ሚና አለው፡፡

‎የሚወክለንን ፓርቲ የምንመርጥበትን ቀን በጉጉት እየጠበቅን ነው ያሉት ነዋሪዎቹ÷ ‎ለሀገር ግንባታና ዴሞክራሲ የአንድ ሰው ድምፅ ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

‎ሀገርን የሚጠቅምና የሚገነባ እንዲሁም የዜጎችን ሕይወት ያሻሽላል የሚሉትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ ቁርጠኛ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

‎ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንደሚወጡም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በ‎አብደላ አማን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.