Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሁለት አዳዲስ የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎቶችን ስራ አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለአዲስ አበባ 10ኛ እና 11ኛ የሆኑ ሁለት የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎቶችን በይፋ መርቀው ስራ አስጀምረዋል።

ከንቲባዋ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፥ በ2018 በተገባው ቃል መሰረት በአዲስ አበባ 11 የአዲስ መሶብ ማዕከላትን መክፈት ችለናል ብለዋል።

ማዕከላቱ በቃሊቲ እና በለሚ ኩራ ክፍለከተሞች መገንባታቸውን ጠቅሰው፤ የማዕከላቱ ወደስራ መግባት የተገልጋዮችን እንግልት በመግታት ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችል አብራርተዋል።

የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎቶት የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደትን ማዘመን የተቻለበት መሆኑን ተናግረዋል።

የመሶብ ማዕከላቱ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የተደራጁ በመሆናቸው ማንኛውም የከተማዋ ነዋሪ በፈለገው ማዕከል አገልግሎት ማግኘት ይችላል ያሉት ከንቲባዋ፤ ዲጂታል ቴክኖሎጂዎቹ በሀገር ውስጥ አቅም የበለጸጉ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ማዕከላቱ ከ50 በመቶ በላይ የመንግሥት አገልግሎቶችን የሚሰጡና ለእናቶችና ህፃናት የተመቸ የመጫወቻ ስፍራም እንዳካተቱ ገልጸዋል።

መሠል ዘርፎችን ማልማት የኢትዮጵያን የብልፅግና ጉዞ እንደሚያጠናክሩ ገልጸው፤ ህዝብና መንግሥት ይበልጥ በተቀናጁ ቁጥር ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንደሚያስችል አመልክተዋል።

በሔኖክ ለሜ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.