Fana: At a Speed of Life!

በቬንዙዌላ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 235 ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በቬንዙዌላ መዲና ካራካስና ላ ጓይራ ግዛት በተከሰተው ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የሟቾች ሰዎች ቁጥር 235 ደርሷል፡፡

አደጋውን ተከትሎ በፍርስራሽ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን የማፈላለግና የነፍስ አድን ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸው ተገልጿል፡፡

7 ነጥብ 2 እና 7 ነጥብ 5 ሬክትር ስኬል ሆኖ በተመዘገበው የርዕደ መሬት አደጋ የሟቾች ቁጥር እስካሁን 235 የደረሰ ሲሆን 4 ሺህ 300 ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

በተጨማሪም በወደብ ከተማዋ ላ ጓይራ 250 የመኖሪያ ቤቶች በአደጋው መውደማቸው ነው የተገለጸው፡፡

በአደጋው የሞቱ ሰዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ሲገለጽ፥ በርካታ ሰዎች ከአደጋው ለመሸሽ አካባቢያቸውን ለቀው እየወጡ መሆናቸው ነው የተገለጸው፡፡

የሀገሪቱ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ዴልሲ ሮድሪጌዝ አደጋውን ተከትሎ የነፍስ አድን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ ሀገራት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አሜሪካ 150 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ቃል የገባች ሲሆን፥ የነፍስ አድን ስራውን ለማገዝ የነፍስ አድን ቡድን ወደ ካራካስ መላኳን አስታውቃለች፡፡

በሚኪያስ  አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.