Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ የሚገኙ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኖሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ የሚገኙ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት በእንጦጦ ፓርክ የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሂደዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራን ጨምሮ በርካታ የውጭ ሀገራት አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶችና የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።
አምባሳደር ሀደራ አበራ በዚሁ ወቅት፥ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ ባከናወነቻቸው ተምሳሌታዊ ተግባራት በዓለም አቀፍ መድረኮች እውቅናን ማግኘቷን አንስተዋል፡፡
የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኩመራ ዋቅጅራ በበኩላቸው፥ የአረንጓዴ ዐሻራ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ኃላፊነትን የመወጣት ብቻ ሳይሆን የአንድነት ውጤት ማሳያ ሆኗል ነው ያሉት፡፡
ተፈጥሮ ላይ መዋዕለ ንዋይን ማፍሰስ ለሰላምና ልማት መረጋገጥ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አስረድተዋል።
በአሸናፊ ሽብሩ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.