Fana: At a Speed of Life!

በባንጃ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ባንጃ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰባት ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡

አደጋው ከቅዳማጃ ከተማ ወደ አስኩና በመጓዝ ላይ የነበረ ባጃጅ ዛሬ ቀን 8 ሰዓት ላይ ከሲኖትራክ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው የደረሰው፡፡

በአደጋው አሽከርካሪውን ጨምሮ የሰባት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የባንጃ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር የሻምበል ገበየሁ ተናግረዋል፡፡

በባጃጁ ውስጥ የነበረች አንዲት ሕጻን ልጅ በሕይወት መትረፏን ጠቁመው÷ጉዳት የደረሰባቸው ሁለት ዜጎች አቅራቢያ ወደሚገኝ ሆስፒታል መላካቸውን ገልጸዋል፡፡

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ እንደሆነ መጠቆማቸውንም የዞኑ ኮሙኒኬሽን መምሪያ ባለሙያ በላይነሽ አበበ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.