Fana: At a Speed of Life!

ብሔራዊ የአምራች ኢንዱስትሪ የሃብት ልየታ ጥናት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ያሉ እምቅ ሃብቶችን በመለየት ጥቅም ላይ ማዋል የሚያስችል የብሔራዊ አምራች ኢንዱስትሪ የሃብት ልየታ ጥናት ይፋ ተደርጓል።

ጥናቱ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች፣ ሚኒስትሮች እና የተቋማት ኃላፊዎች በተገኙበት ነው በዛሬው ዕለት ይፋ የሆነው፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ጥናቱ በአምራች ዘርፍ መሰማራት ለሚፈልጉ አካላት በምን ዘርፍ ውጤታማ መሆን እንደሚቻል ምክረ ሃሳብ ለመስጠት ያግዛል፡፡

በመጪዎቹ 5 ዓመታት በሀገር አቀፍ ደረጃ ብሎም በክልሎች ያሉ ሀብቶችን በውጤታማነት መጠቀም የሚያስችል መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

ኢንዱስትሪ ሲቋቋም በእውቀት ላይ ተመስርቶ ውጤታማ መሆን በሚያስችል መንገድ መሆን እንዳለበት ተጠቁሟል።

ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ ምግብና መጠጥ፣ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ፣ ኮንስትራክሽን እና ኬሚካል በትኩረት የሚሰራባቸው ዘርፎች እንደሆኑ ተጠቅሷል።

በጥናቱ እንደ አካባቢዎቹ አቅም የኢኮኖሚ ኮሪደሮች የተለዩ ሲሆን÷ የሃይል አቅርቦትና የጉምሩክ እንዲሁም መሰል ጉዳዮች ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገቡ ዘርፎች መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

በኤፍሬም ምትኩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.