Fana: At a Speed of Life!

ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ሲዳማ ቡናን 2 ለ 0 በማሸነፍ የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ ሆኗል፡፡

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ የወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ኮንኮኒ ሀፊዝ እና በየነ ባንጃ አስቆጥረዋል፡፡

ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ዋንጫ ሻምፒዮን ሆኗል፡፡

የሊጉ ሻምፒዮን ሲዳማ ቡና በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ዋንጫ ማሳካት የሚችልበትን ዕድል ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.