Fana: At a Speed of Life!

 ችግሮችን በምክክር የመፍታት ጥበብ …

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክክር ያልታዩ ሀሳቦች የሚታዩበት፣ ሀገር ለመገንባት ውይይት የሚደረግበትና የጋራ መፍትሔ የሚቀመጥበት መሳሪያ ነው፡፡

ዛሬ ላይ የትኛውም ኢትዮጵያዊ በዓለም ሕዝብ ፊት በማንነቱ የሚኮራው ቀደምት ኢትዮጵያውያን አባቶቹ ባስቀመጡለት በጎ አሻራ ነው።

የተሳሳቱ ትርክቶች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብርን በማበላሸት፤ የኢትዮጵያን ገጽታ ለማጠልሸት መንስኤ እየሆኑ መጥተዋል፡፡

እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ትልቁን ሚና የሚጫወተው ደግሞ መመካከር እና በጠረጴዛ ዙሪያ መወያየት ነው፡፡

ምክክር ያልታዩ ሀሳቦች የሚታዩበት፣ ለመግባባትና ሀገር ለመገንባት ውይይት የሚደረግበት እንዲሁም ለጋራ ችግሮች የጋራ መፍትሔ የሚቀመጥበት መሳሪያ መሆኑ ይታመናል፡፡

የሥልጣኔ መገለጫ ከሆኑት ነገሮች ውስጥ አንዱ ችግሮችን በውይይት የመፍታት ጥበብ ነው፡፡

የሀሳብ ልዩነቶችን እና አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት ለቀጣይ ትውልድ የተሻለች ሀገር ለማስረከብ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡

ኢትዮጵያ የተለያዩ ማንነት ባላቸው ሕዝቦች የተገነባች ሀገር እንደመሆኗ ጠላቶቿ ይህን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ሕብረተሰቡን ለማጋጨት እና ለጸብ ለማነሳሳት ሲጠቀሙበት ቆይተዋል፡፡

እንዲሁም ልዩነቶቻቸውን እንደ ስጋት ምንጭ እንዲያዩ፣ እርስ በርስ እንዲፈራሩ እና እንዳይግባቡ የተዛቡ ትርክቶችን ለመፍጠር ሲተጉ፤ ከውስጥ ያሉ ባንዳዎች ደግሞ ፍላጎታቸውን በማስኬድ ተባባሪ ሲሆኑ ይስተዋላል፡፡

ምክክር ዜጎች ተሰሚነት እንዳላቸው፣ በሀሳባቸው ለውጥ ማምጣት እንደሚችሉ እንዲያምኑ ከማድረጉ ባሻገር በመንግሥት እና በሕዝብ መካከል ያለውን መተማመን ያጠናክራል፡፡

በውይይት ችግሩን መፍታት የቻለ ሕብረተሰብ፣ ለሰላም ዘብ የሚሆን በግጭትና በጦርነት ከሚደርሱ ውድመቶች ሀገርን የሚታደግ እንደሚሆን ይታመናል፡፡

በተጨማሪም ለሀገር ጥቅም በጋራ የሚቆም፣ ለዲፕሎማሲ ከፍታ የሚተጋ፣ ዳር ቆሞ ከመመልከት ይልቅ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለማሳደግና ለልማት የሚተባበር ይሆናል።

ዛሬ ላይ ችግሮችን በምክክር መፍታት ለሚቀጥለው ትውልድ የተሻለች ሀገርን ለማስተላለፍ ይረዳል፡፡

በቤተልሔም ግርማ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.