ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡- On Aug 3, 2026 41 ባለፉት ሰባት ዓመታት በተከታታይ ሳናቋርጥ ክረምቱን በሙሉ ዛፍ በመትከል ኢትዮጵያን ለማልበስ፣ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል። የዚህ ጥረት ዋነኛ ዓላማ ኢትዮጵያ መበልጸግ፣ መብላት፣ መለወጥ፣ ማደግ፣ መሰልጠን አለባት የሚል ምኞት፣ ህልም፣ መሻት ብዙ ኢትዮጵያዊያን አላቸው። እንደዚህ ያለው ትላልቁ ህልም ሊሳካ የሚችለው አስተማማኝ መሰረት ከተጣለ ብቻ ነው። በኢኮሎጂ መሰረት መጣል ማለት አፈር፣ ውሃ፣ ተራራን መጠበቅ ሲቻል ነው፤ ከህግ አንጻር መሰረት መጣል ማለት ህዝብ ተወያይቶ አሳታፊ የሆነ አስተማማኝ ህግ ማስቀመጥ ሲቻል ነው። እነኚህ መሰረቶች ሳይጣሉ እዚህ ላይ የሚገነባ ማንኛውም ግንብ በማንኛውም አጋጣሚ ፈራሽ ሊሆን ይችላል። አሁን እየሰራን ያለነው ለልጆቻችን ነው፣ ተስፋ ነው የምንተክለው፣ ነገን ነው የምንተክለው፣ ኢትዮጵያን ነው ምናልበሰው፤ ይህ ደግሞ የሚሆነው በትብብር ነው፣ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በጋር ወጥቶ በሚያደርገው ጥረት ነው ይህ ጥረት ብዙዎች እውቅና ሰጥተውት የኢትዮጵያን መንገድ ለመከተል ጥረት እያደረጉ ይታያሉ። ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ባደረገችው ጥረት የዓለም መንግሥታት እውቅና ሰጥተው ሽልማት ብቻ ሳይሆን የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ-32) ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲዘጋጅ ወስነዋል። ኮፕ-32 ማለት በዓለም አካባቢን በሚመለከት በጣም ትልቁ ስብሰባ የሚካሄድበት ነው። ስብሰባው ከ80 ሺህ እስከ 100 ሺህ ሰዎች የሚሳተፉበት እንዲሁም ቢያንስ እስከ 100 መሪዎች ይሳተፉበታል። እንደዚህ ዓይነቱን ትልቅ በዓል ኢትዮጵያ አዘጋጅታ አታውቅም፤ ከሰሃራ በታች ያሉ ሀገራ አዘጋጅተው አያውቁም፤ ለኛ ትልቁ ብስራት የሚሆነው የለበሰች፣ ያማረች፣ እያደገች ያለች፣ ተስፋ ያላት ኢትዮጵያን ከብዙ ንግግር በላይ ገልጠን ለማሳየት የኛን ተጨባጭ ልምድ ለማካፈል ትልቅ መድረክ ነው፣ በዛው ልክ ደግሞ የምናገኛቸው ጥቅሞች በርከት ያሉ ናቸው። እኛ ኮፕ-32ን አስታከን ዓመቱን ሙሉ ኢትዮጵያን እገነባለን፣ እንተክላለን፣ እናጸዳለን፣ እንገነባለን። ኢትዮጵያን እየገነባን ምክንያት አድርገን በመጠቀም የተባበረ ህዝብ መሰረት መጣል እንደሚችል፣ የተባበረ ህዝብ ሀገር መገንባ እንደሚችል ማሳያ እንደሚሆን ተስፋ አለኝ። ይህንን ስራ ስንሰራ ለልጆቻችን አንድ ማስታወሻ እየተውን፣ ቅርስ እያስቀመጥን እንደሆነ እያሰብን እንስራ፤ ዛፍ ለዛሬ ትርጉም የለውም ለነገ ግን ትርጉሙ ብዙ ነው፣ ምግብ ነው፣ ጥላ ነው፣ ውበት ነው ከዛም ባሻገር የሚሸረሸር፣ የሚጠፋ ሀብታችንን ጠባቂ ዘብ ነው። ዛሬ 800 ሚሊየን ችግኝ ጀግኖች ኢትዮጵያዊያን ለመትከል ከጠዋት ጀምሮ እየተረባረቡ ይገኛሉ፤ ደጋግመን በመትከል ይህ ያልነውን ቃል እንደምንፈጽም ሙሉ እምነት አለኝ፣ በርቱ ተስፋን ትከሉ። በአቤል ነዋይ 41 Share FacebookTwitterTelegramWhatsAppEmailViberPrint