አረንጓዴ ዐሻራ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ልማት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ነው – አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ለኢትዮጵያ ዘላቂ ልማት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ነው አሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፡፡
አፈ ጉባዔው በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ÷ ባለፉት ሰባት ዓመታት በተከናወኑ የአረንጓዴ ዐሻራ ሥራዎች በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸው አንስተዋል፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት በተጀመረው መርሐ ግብር ሴቶች፣ ወጣቶች፣ ህፃናት፣ ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ አካል ጉዳተኞች እና ሌሎች የማሕብረሰብ ክፍሎች በንቃት እየተሳተፉ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በዚህም በምርትና ምርታማነት፣ በአፈር ለምነት፣ በደን ሽፋን፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በውሃማ አካላት እና በሌሎች ዘርፎች ላይ ስኬት ማስመዘገብ መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡
መርሐ ግብሩ ከተፈጥሮ ጋር መግባባት የምንፈጥርበትና ዘላቂ ልማትን የምናረጋግጥበት ዋነኛ መሳሪያ ነው ሲሉም አውስተዋል፡፡
በሚኪያስ አየለ