Fana: At a Speed of Life!

የመደመር መንግሥት ዜጎችን ማዕከል ያደረገ የዲፕሎማሲ መርህ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአንድ ሀገር የውጭ ፖሊሲ ስኬት የሚለካው በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ባለው ተጽዕኖ ብቻ ሳይሆን፣ የዜጎችን ክብርና ደህንነት በሀገርም ውስጥ ሆነ በውጭ ሀገራት በማስጠበቅ ጭምር ነው፡፡
ባለፉት ስምንት ዓመታት የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ችግሮች ሲፈጠሩ ብቻ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ችግሮችን አስቀድሞ በመለየት ርምጃ የሚወስድ በጋራ እድገት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡
ይህ መዋቅራዊ ሽግግር የሀገር ውስጥ ልማት እና ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲያዊ ለውጦች የማይነጣጠሉ መሆናቸውን በአግባቡ ያሳያል፡፡
በሀገር ውስጥ የሚከናወኑ የልማት እንቅስቃሴዎች በዓለም የዲፕሎማሲ መድረክ ላይ ተአማኒነትን እና ዓለም አቀፍዊ አጋርነትን በማጠናከር ከፍተኛ የኢኮኖሚ እድገትን ለማምጣት የተቀረጸ የዲፕሎማሲ ስልት ነው።
ባለፉት ስምንት ዓመታት የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ አጋርነት ለረጅም ዓመታት ከምዕራብውያን ሀገራት ጋር የነበረን ከማስቀጠል በተጨማሪ ከባህረ ሰላጤው ሀገራት እና በእስያ ከሚገኙ የኢኮኖሚ ኃይሎች ጋር ጠንካራ ትስስር ፈጥሯል።
የኢትዮጵያ አዲሱ ዲፕሎማሲ ከፍትኛ ትኩረት ከሰጠባቸው ጉዳዮች አንዱ የዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ነው፡፡
በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በስደት ያሉትን በማወያየት እንዲሁም የታሰሩትን በማስፈታት ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ድል አስመዝግበዋል፡፡
የመደመር መንግሥት ዜጎችን ማዕከል ያደረገ የዲፕሎማሲ መርህን በመከተል በውጭ የሚኖረውን ትውልደ ኢትዮጵያ ማህበረሰብ እንደስጋት ከማየት ይልቅ ለሀገር ግንባታ እንደ አጋር የመመልከት አወንታዊ ለውጥ አድርጓል።
ከተለያዩ ሀገራት ጋር የተፈረሙ የሰው ኃይል ስምሪት ስምምነቶች የዜጎችን መብትና ክብር ለመጠበቅ የተደረጉ ጠንካራ ተግባራት ናቸው።
የዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ትኩረት በጥሩ ሁኔታ ላይ ያሉ ትውልደ ኢትዮጵያን ላይ ብቻ ሳይሆን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት ለመመለስም ሰፊ ዕድል ፈጥሯል፡፡
ለዜጎች የተሰጠው ትኩረት ወደ ሀገር መመለስ ብቻ ሳይሆን መልሶ ማቋቋምን ያካተተ ነው።
ዜጎች ገቢ በሚያስገኙ ስራዎች ላይ እንዲሳተፉ የሚያግዝ የፋይናንስ እና የክህሎት ድጋፍ ማግኘታቸው በሀገራቸው ተስፋ እንዲሰንቁ የሚያደርግ ወሳኝ ተግበር በመሆኑ መንግሥት በትኩረት እየሰራበት ይገኛል፡፡
በአብረሃም አበራ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.