Fana: At a Speed of Life!

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕ/ር) የምክክር ጉባዔውን አሁናዊ ሒደት አስመልክተው በሰጡት መግለጫ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-

👉 በምክክር ሂደቱ መጀመሪያ ላይ ሀሳቦች በሚበታተኑበት ምዕራፍ ጭቅጭቆች እና አለመግባባቶች መፈጠራቸው ተፈጥሮአዊ እና አግባብ ነው።

👉 ተመካካሪዎች ተጨቃጭቀው ወደ መሰባሰብ ምዕራፍ ሲደርሱ የግል ሀሳቦቻቸውን በመተው ሀገርን ያማከሉ የጋራ ሀሳቦችን እያደራጁ ይሄዳሉ።

👉 በጣም ያጨቃጭቃሉ ተብለው ይፈሩ የነበሩ አጀንዳዎችና ጥያቄዎች ተሳታፊዎች የጋራ እና አንድ የሚያደርጉን ናቸው በማለታቸው ወደ መሀል እየመጡ ይገኛሉ።

👉 በምክክሩ ከ60 በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሃይማኖት ተቋማት እና በርካታ የማህበረሰብ ተወካዮች በመኖራቸው የየራሳቸው አጀንዳዎች ቀድመው እንዲቀርቡላቸው የሚፈልጉ አካላት አቤቱታዎችን ያቀርባሉ።

👉 ኮሚሽኑ ቅሬታዎችን የሚቀበሉ ከፍተኛ ባለሙያዎች ያሉት ሲሆን፤ ጉዳዮቹን አቀናጅተው ለሊድ ኮሚሽነሮች እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ለኮሚሽኑ ምክር ቤት በማቅረብ ውሳኔ እንዲያገኙ ያደርጋሉ።

👉 ኮሚሽኑ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ከሃይማኖት መሪዎች ጋር በተናጠል ተገናኝቶ በመወያየቱ አብዛኞቹ ትልቅ ድጋፍ እየሰጡ ይገኛሉ።

👉 ምክክር አዲስ የውይይት ባህል በመሆኑ ከተለመደው የኃይል ወይም “ካልተሰማሁ ጥዬ እወጣለሁ” ከሚል ግትር አካሄድ ወጥቶ ሁለቱንም ወገኖች አሸናፊ ወደሚያደርግ ሀሳብ መምጣት ያስፈልጋል።

👉 የተማሩ አካላትም ሆኑ ከአርሶ አደር እና አርብቶ አደር ማህበረሰብ የመጡ ተወካዮች የእውቀት ባለቤቶች በመሆናቸው ሁሉም እኩል መደመጥ አለባቸው።

👉 እስካሁን ባለው ሂደት ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ የመጡ ተሳታፊዎች ሂደቱን በጥሩ ሁኔታ እየተከታተሉ ይገኛሉ።

👉 አንዳንዶቹ አጀንዳዎች ጊዜ የሚፈጁና ወደ ቀጣይ ትውልድም ሊሸጋገሩ የሚችሉ ጥያቄዎች ሊሆኑ ይችላሉ፤ ምክክር ይጀምራል እንጂ በማግስቱ የሚያልቅ አይደለም።

👉 በአሁኑ ወቅት 4 ሺህ ተመካካሪዎች በስምንት ቦታዎች አምስት አምስት መቶ ሆነው እየተመካከሩ ይገኛሉ።

👉 አልፎ አልፎ በሚሰሙ ድምጾች ወይም ሰጣ ገባዎች ውጤቱ አያምርም ብሎ መገመት ተገቢ አይደለም።

👉 በሚቀጥሉት አንድ እና ሁለት ሳምንታት ውስጥ ከ4 ሺህ ተሳታፊዎች ጋር የሚደረጉ ስራዎችን የማጠናቀቅ ተስፋ አለ።

👉 ከዚህ በኋላ የመጡትን ሀሳቦች አጠናቅሮ ለሚተገብረው አካል መላክ እና ትግበራውን እየተከታተሉ ለህዝብ ማሳወቅ የኮሚሽኑ ቀጣይ ትልቅ ስራ ይሆናል።

በዮናስ ጌትነት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.