Fana: At a Speed of Life!

ሀገራዊ ምክክር የሰላም፣ የፍትህና የብልጽግና ጉዞን ለማጠናከር

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የረጅም ዘመን የነጻነት፣ የባህልና የታሪክ ባለጸጋ የሆነች ሀገር ብትሆንም ከትውልድ ወደ ትውልድ የተሻገሩ ልዮነቶችና አለመግባባቶች በየጊዜው የግጭት መንስኤ ሲሆኑ ሰንብተዋል፡፡

በእነዚህ ውስብስብ ሀገራዊ ችግሮች መካከል ለዘላቂ ሰላምና ሀገራዊ መግባባት እንደ ትልቅ የመፍትሔ መንገድ ሆኖ የመጣው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ነው።

በሀገራዊ ምክክሩ የፖለቲካ ልሂቃን፣ የሁሉም ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ተወካዮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሲቪክ ማህበራት እና የዳያስፖራው የህብረተሰብ ክፍሎች በጋራ በመቀመጥ መሠረታዊ በሚባሉ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በግልጽ የሚያወያዩበትና የጋራ መግባባት የሚፈጥሩበት ሂደት ነው።

በኢትዮጵያ የፖለቲካ ስነ ምህዳር ውስጥ የጋራ እሴቶችን በተለያየ መንገድ የመተርጎም ክፍተት የነበረ ሲሆን ምክክሩ የወል ትርክትን ከመገንባት አንጻር ትልቅ ሚና ይጫወታል።

ሂደቱ በግጭትና በኃይል ሀሳቤ ይሰማልኝ ከሚል ጊዜው ያለፈበት አካሄድ ይልቅ በሰለጠነ መንገድ በውይይትና በዴሞክራሲያዊ መንገድ ልዩነቶችን የማስተናገድ ባህልን አዳብሯል።

ውድ የኢትዮጵያ ልጆች ከያሉበት ተሳባስበው እጆች ለግጭት ሳይሆን ለወንድማማችነት ተዘርግተው በረሀና ጫካን ሳይሆን፤ የጠረጴዛ ዙሪያን መርጠው የኔን ወደ እኛ ሀሳብ አምጥተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚ ፈታኝ የሆኑ ጊዜያትን ብታሳልፍም፣ ከማቀራረብ ይልቅ ሲያራርቁ፤ ከማነጋገር ይልቅ ጦር ሲያማዝዙ፤ የነበሩ የችግር አዙሪቶችን ለመሻገርና የሰላም፣ የፍትህና የብልጽግና መንገድን ለማንጠፍ ሀገራዊ ምክክሩ ታላቅ ታሪካዊ ዕድል ነው።

በመልካም ፈቃዱ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.