Fana: At a Speed of Life!

በሥራና ክህሎት ዘርፍ ለቀጣይ የልማት ጉዞ ጠንካራ መሠረት ተጥሏል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት አምስት ዓመታት በሥራና ክህሎት ዘርፍ ለቀጣይ የልማት ጉዞ ጠንካራ መሠረት የሚሆኑ ተግባራት ተከናውነዋል አሉ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ካሚል።
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአምስት ዓመታት አፈጻጸም ለመገምገምና በወደፊት አቅጣጫዎች ላይ ለመምከር ያለመ መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡
ሚኒስትሯ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ባለፉት አምስት ዓመታት የቴክኒክና ሙያ ሥልጠናን ከዘመኑ አስተሳሰብና ከገበያ ፍላጎት ጋር ለማጣጣም የሚያስችሉ መሠረታዊ ሥራዎች ተከናውነዋል።
በዚህም ከአካባቢው የኢኮኖሚ ሀብትና ከኢንዱስትሪ ፍላጎት ጋር የተጣጣመ የሰው ኃይል ለማፍራት እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ለቀጣዩ የልማት ጉዞ የግሉ ዘርፍ በኢኮኖሚው ውስጥ የሚኖረውን ቀዳሚ ሚና ለማጠናከር የሥልጠና ሥርዓቱን ከኢንዱስትሪው ጋር ማጣጣም ዋነኛ ትኩረት መሆኑንም አስረድተዋል።
የዲጂታል 2030 ስትራቴጂን ለማሳካት ዜጎችን በዲጂታል ክህሎት ማስታጠቅ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
የሥራ ፈጠራን ማስፋትና ማበረታታት የቀጣይ አቅጣጫ ዋና አካል ነው ማለታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.