Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆቿ ጽናትና ተጋድሎ በድል የተሻገረች ሀገር ናት – ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በታሪኳ ከውስጥም ሆነ ከውጭ የተሰነዘሩባትን ፈተናዎች በጀግኖች ልጆቿ ጽናትና ተጋድሎ በድል ተሻግራ የኖረች ሀገር ናት አሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ምዕራብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል “የጽናት ቀን” በቦንጋ ከተማ በድምቀት ተከብሯል።
ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት ፥ ኢትዮጵያ ያጋጠሟት ሀገራዊና ክልላዊ ፈተናዎች በሙሉ በህዝብና በአመራሩ የጋራ ጽናት ወደ ታላላቅ ድሎችና የልማት እድሎች ተቀይረዋል ብለዋል።
የታላቁ ሕዳሴ ግድብ፣ የስንዴ ምርታማነት፣ የኮሪደር ልማትና የቱሪዝም መዳረሻ ስራዎች በስኬት ተጠናቅቀው ለነገው ትውልድ የሚሆን ትልቅ ዐሻራ እያሳረፉ ይገኛሉ ነው ያሉት።
ርዕሰ መስተዳድሩ ሁላችንም በየተሰማራንበት ሙያና የስራ መስክ ሀገርንና ክልልን ወደተሻለ ደረጃ የማሸጋገር አደራ አለብን ሲሉም አሳስበዋል።
በዳዊት ጎሳዬ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.