Fana: At a Speed of Life!

ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን ለመገንባት ባለድርሻ አካላት በትብብር ሊሰሩ ይገባል-አቶ ኢሳያስ ጂራ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ)ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን ለመገንባት የእግርኳስ ባለድርሻ አካላት በትብብር ሊሰሩ ይገባል አሉ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ፡፡

ለሶስት ተከታታይ ጊዜ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት በመሆን የተመረጡት አቶ ኢሳያስ ከፋና ስፖርት ጋር ባደረጉት ቆይታ÷ በሃላፊነት በቆዩባቸው ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያን እግር ኳስ ውስጥ በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን አንስተዋል፡፡

ለአብነትም ባለፉት ዓመታት ፌዴሬሽኑ ከሊግ ኩባንያው ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ የቀጥታ ስርጭታ ሽፋን እንዲያገኝ ማድረግ መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡

ያለፉት ስምንት ዓመታት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ማለፍ የቻለበት እንዲሁም ከስምንት ዓመታት በሁዋላ በቻን ውድድር መሳተፍ የቻለበት  ዓመታት እንደነበሩ ጠቅሰዋል፡፡

በተጨማሪም የሊጉን አወቃቀር ማስተከካከል ተችሏል ያሉት ፕሬዚዳንቱ ÷የኢትዮጵያ እግር ኳስ በአፍሪካ እና በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና እንዲያገኝ ማድረግ መቻሉን አብራርተዋል፡፡

በዚህም ከ25 ሚሊየን ዶላር  በላይ ገቢ ማግኘት ተችሏል ነው ያሉት፡፡

ነገር ግን አሁንም እግርኳስ በሚፈለገው ደረጃ እንደማይገኝ በመጠቆም፣ጠንካራ ሊግ እና ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን ለመገንባት የእግርኳስ ባለድርሻ አካላት በትብብር ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎት እና የብሔራዊ ቡድኑ አቋም አይገናኝም ያሉት ፕሬዚዳንቱ ÷በእግርኳሱ ለውጥ ለማምጣት የጋራ ጥረት ማድረግ እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል፡፡

እግር ኳሱን ለማሳደግ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የረጅም ጊዜ እቅድ አውጥቶ እየሰራ እንደሚገኝም አመላክተዋል፡፡

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.