ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በነፃ ተለቀቁ
አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 28 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሁከትና አመጽ በማስነሳት በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ ወንጀል ተጠርጥረው በፖሊስ ምርመራ ሲደረግባቸው የነበሩት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በነፃ ተለቀቁ።
የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ አራዳ ምድብ ተረኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት መርማሪ ፖሊስ በኢንጂነር ይልቃል ላይ ሲያከናውን የነበረውን ምርመራ ማጠናቀቁን እና መዝገቡንም ለዐቃቤ ህግ መስጠቱን ለችሎቱ መግለፁን ተከትሎ ችሎቱም አቃቤ ህግ በ10 ቀን ውስጥ ክስ እንዲመሰርት ነሃሴ 13 ቀን 2012 ዓመተ ምህረት ብይን ሰጥቶት ነበር፡፡
ሆኖም አቃቤ ህግ በተሰጠው የክስ መመስረቻ ጊዜ ውስጥ ክስ መመስረት አለመቻሉን እና ሌላ ማጣራው መስረጃ አለኝ ማለቱን ተከትሎ ኢንጂነር ይልቃል በነፃ ተለቀዋል።
በታሪክ አዱኛ