Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ በሚገነባው የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ በሚገነባው የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ዝግጅትና ቀጣይ የትግበራ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል፡፡
የኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ኮሚሽነር አብረሃም በላይ (ዶ/ር) ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ከጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በሀገሪቱ ሊገነባ የታቀደውን የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት እውን ለማድረግ በሚያስችሉ የሁለትዮሽ ስምምነቶች ዝግጅትና በቀጣይ የትግበራ አቅጣጫዎች ላይ ምክክር አድርገዋል።
በዚህም ፕሮጀክቱን በብቃት ወደ መሬት ለማውረድ የሚረዱ ሀገራዊ ቅንጅቶችን አጠናክሮ መቀጠል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ አቅጣጫ ተቀምጧል።
ይህ መድረክ የሀገሪቱን የኢነርጂ ዋስትና ማረጋገጥና በዘርፉ ሀገራዊ አቅም መገንባት የሚያስችሉ ስትራቴጂያዊና ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴዎችን በበለጠ ለማፋጠን ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ ለታዳሽና አስተማማኝ የንጹህ ኃይል ልማት ያላት ጽኑ ቁርጠኝነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠነከረ መምጣቱን የሚያሳይ ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን ኮሚሽኑ ገልጿል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.