Fana: At a Speed of Life!

ማለዳ ፎም ያስጀመረው በቂ እረፍት ለጤና ሀገር አቀፍ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ

በፈጠራዊ ታሪክ አቀራረብና በሕዝብ ተሳትፎ ለማስፈጸም ማለዳ ፎም እረፍት እንዲሳካ የተሰኘውን የድርጅታዊ ማኅበራዊ ኃላፊነት ዘመቻ ከሰውመሆን ፊልምስ ጋር የአጋርነት ስምምነት በመፈራረም አስጀምሯል፡፡

ዘመቻው ትክክለኛና በቂ እረፍት ለጤና፣ ለትምህርት፣ ለምርታማነት፣ ለግል አፈጻጸም፣ ለቤተሰብ ደህንነት እና ለሀገር ልማት ያለውን አስፈላጊነት በተመለከተ የሕዝብ ግንዛቤን ለማሳደግ የተዘጋጀ ነው።

በአዲስ አበባ በተካሄደው የመክፈቻ ፕሮግራሙ የፋይናንስ ተቋማት፣ የንግድ አጋሮች እና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

በዝግጅቱ ማለዳ ፎም ከሰው መሆን ፊልምስ ጋር ዘመቻውን በፈጠራዊ ታሪክ አቀራረብ፣ በድምፅና ምስል ይዘቶች እና በሕዝብ ተሳትፎ ለማስፈጸም የአጋርነት ስምምነት ተፈርሟል።

“በህይዎትዎ ይበልጥ ዋጋ የሚሰጡት ነገር ምንድን ነው? “በህይዎትዎ ይበልጥ ዋጋ የሚሰጡት ነገር ምንም ቢሆን ምንም እንዲሳካ ተገቢ እና ምቹ ዕረፍት ያስፈልግዎታል “ በሚል ዋና መልዕክት የሚመራው ዘመቻ፣ በሕይወት ውስጥ አስፈላጊ የሆኑ ጉዳዮችን ለማሳካት የራስን ጤናና ደህንነት መጠበቅ እና ለትክክለኛ እረፍት ቅድሚያ መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ያስገነዝባል።

ተማሪዎች የትምህርት ግቦቻቸውን ለማሳካት ይጥራሉ፤ ወላጆች ለልጆቻቸው የተሻለ ወደፊት ለመፍጠር ይተጋሉ፤ ባለሙያዎች በሙያቸው ለመሻሻል ይሰራሉ፤ ሥራ ፈጣሪዎችም የንግድ ሥራቸውን ያሳድጋሉ። እነዚህ ዓላማዎች ትጋትና ቁርጠኝነት ቢፈልጉም፣ ለጤና፣ ለደህንነት እና ለበቂ እረፍት ትኩረት መስጠትንም ይጠይቃሉ።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የግንዛቤና የሕዝብ ተሳትፎ ዘመቻ የዘመቻውን መልዕክት ለተለያዩ ታዳሚዎች ለማድረስ ማለዳ ፎም የሕዝብ ግንዛቤን፣ የማኅበረሰብ ተሳትፎን፣ የፈጠራ ሥራዎችን እና ቀጥተኛ የህዝብ ተሳትፎን የሚያቀናጁ ተግባራትን ለማከናወን ማቀዱ ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.