Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁና የልማት ክፍተቶች እንዲሞሉ በትኩረት ይሰራል – አቶ ፍቅሬ አማን

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የተጀመሩ ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁና የልማት ክፍተቶች እንዲሞሉ የመደመር መንግሥት በትኩረት ይሰራል አሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ፍቅሬ አማን።

ርዕሰ መስተዳድሩ ይህንን ያሉት ከቤንች ሸኮ ዞን የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ህዝባዊ ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው።

በውይይቱም የመደመር መንግሥት ባለፉት ስምንት ዓመታት የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በርካታ ሥራዎችን ማከናወኑንና ሰፋፊ ድሎች መመዝገባቸውን ተናግረዋል።

የመደመር መንግሥት ለህዝብ የቀረበና ህዝብን የሚያዳምጥ በመሆኑ በቤንች ሸኮ ዞን የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁና ክፍተቶች እንዲሞሉ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።

አቶ ፍቅሬ አማን አክለውም ፥ ክልሉ የብዝሃነት ማዕከልና የጸጋ ምድር መሆኑን በመጠቆም ያለውን አቅም አቅናጅቶ በመጠቀም በአጭር ጊዜ ውስጥ ብልጽግናን ማረጋገጥ እንደሚቻል አስረድተዋል።

የመደመር መንግሥት ሰላምን፣ ብልጽግናንና ጠንካራ ተቋማትን በመገንባት እንደሚያምንና በምርጫ ወቅት ህዝቡ ያነሳቸውን ጥያቄዎችና ብልጽግና ፓርቲ የገባቸውን ቃሎች በተግባር ለመመለስ እንደሚሠራም አረጋግጠዋል።

በተስፋዬ ምሬሳ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.