Fana: At a Speed of Life!

‎መከላከያ ሰራዊት ሰባት የፅምዶ ትብብር ቡድኖችንና ሶስት የጀርባ የውጭ ኃይሎችን አሸንፏል – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ህገ ወጡ ህወሓት መከላከያን ሊያፈርስ ቋምጦ ነበር ተመትቷል፤ ሠራዊታችን ሰባት የፅምዶ ትብብር ቡድኖችን እና ሶስት የጀርባ የውጭ ኃይሎችን አሸንፏል፤ የቀጣናው አስተማማኝ ሀይል ሆኗል አሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በ119ኛው የመከላከያ ሰራዊት ቀን አከበበር ላይ ባደረጉት ንግግር ፥ ሀገራዊ የመከላከያ ሰራዊቱን ለማፍረስ የታለሙ የተለያዩ የጠላት ሴራዎች ሙሉ በሙሉ መክነዋል ብለዋል።

ሰራዊቱ ሰባት የፅምዶ ትብብር ቡድኖችን እንዲሁም ሶስት የጀርባ የውጭ ኃይሎችን በአሸናፊነት በመምታት አስተማማኝ የቀጣናው ጥንካሬውን ማረጋገጡን አመልክተዋል።

በጫካ መንገድና በአቋራጭ ስልጣን ለመያዝ መሞከር ከንቱ ምኞት መሆኑን የጠቆሙት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ፖለቲካና ስልጣን የሚፈልጉ አካላት ሰላማዊ መንገድን በመከተል ተደራጅተው በምርጫ መወዳደር እንዳለባቸውና ለሰላም እጃቸውን እንዲሰጡም ጥሪ አቅርበዋል።

በተጨማሪም የዓባይ ውሃና የቀይ ባሕር ጥቅም ለኢትዮጵያውያን የተሰጡ ተፈጥሮአዊ ፀጋዎች መሆናቸውንና የመደመር መንግሥትና መከላከያ ሰራዊቱ የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም ከማስከበር ውጭ ሌላ አማራጭ እንደሌላቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።

መከላከያ ሰራዊቱ የጠላትን ሴራ የማፍረስ እንጂ የመፍረስ አቅጣጫ እንደሌለውና ሀገራዊ ሉአላዊነትን የማስከበር ብቃቱ በአስተማማኝ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል።

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.