Fana: At a Speed of Life!

በሳዑዲ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 561 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 561 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 7 ዙር በረራ የተመለሱት 929 ወንዶች፣ 580 ሴቶች እና 52 ህጻናት ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 99 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።

ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየተሰራ ይገኛል፡፡

መስከረም 5 ቀን 2018 በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን ከ111 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ መቻሉን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.