Fana: At a Speed of Life!

985 ግቦች ላይ የደረሰው ሮናልዶ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ አሁንም በግብ አስቆጣሪነቱ ቀጥሏል፡፡
የምን ጊዜም ምርጥ የባሎንዶር አሸናፊ ተብሎ የተመረጠው ክርስቲያኖ ሮናልዶ አሁንም በእግር ኳስ ሜዳ ላይ ሌላ አዲስ ታሪክ እየጻፈ ይገኛል፡፡
የ41 ዓመቱ ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በእግር ኳስ ሕይወቱ 1 ሺህ ግቦች ላይ ለማድረስ የሚያደርገውን ጉዞ አጠናክሮ ቀጥሏል።
ትናንት ምሽት በ12ኛ ሳምንት የሳዑዲ ፕሮ ሊግ አል ናስር ዓል ኹሉድን 5 ለ 3 ሲያሸንፍ ሮናልዶ ሦስት ግቦችን አስቆጥሯል፡፡
ሮናልዶ ትናንት ምሽት 3 ግቦችን ማስቆጠሩን ተከትሎ በእግር ኳስ ሕይወቱ 67ኛውን ሐትሪክ መስራት ችሏል፡፡
ሮናልዶ እስካሁን ድረስ በእግር ኳስ ሕይወቱ ያስቆጠራቸውን ግቦች 985 አድርሷል፡፡
1 ሺህ ግቦች ላይ የመድረስ ህልም ያለው ሮናልዶ ያሰበውን ለማሳካት የሚቀሩት 15 ግቦች ብቻ ናቸው፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.