Fana: At a Speed of Life!

ዲፕሎማቶችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች በትግራይ ክልል የቀድሞ ታጣቂዎች የተሀድሶ ማዕከል ምልከታ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የተባበሩት መንግሥታት ተወካዮችና በኢትዮጵያ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች በትግራይ ክልል የሚገኘውን የቀድሞ ታጣቂዎች ተሀድሶና መልሶ ማቋቋም ስልጠና ማዕከል ጎብኝተዋል።

በክልሉ ቀደም ሲል የተሀድሶና መልሶ ማቋቋም ስልጠና ሲሰጥበት የቆየው የመቀሌ ማዕከል የቀድሞ ታጣቂዎችን ተቀብሎ እያስተናገደ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅት 5 ሺህ 500 የቀድሞ ታጣቂዎች በማዕከላቱ የተሀድሶ ስልጠና እየወሰዱ ይገኛሉ።

የተሀድሶ ስልጠናው የቀድሞ ታጣቂዎችን ወደ ማህበረሰቡ በማቀላቀል፣ መደበኛ ህይወታቸውን እንዲመሩ ከማስቻሉ ባሻገር ለዘላቂ ሀገራዊ ሰላም ግንባታ አዎንታዊ አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑ ተመላክቷል።

በጉብኝቱ የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁንን ጨምሮ የኮሚሽኑ አመራሮች ተገኝተዋል።

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

በግዛቸው ግርማዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.