Fana: At a Speed of Life!

2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) 2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡

ጉባኤው “እድገትን ማስተዳደር፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች የአፍሪካ ኢኮኖሚ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ንድፍ አውጪዎች ናቸው” በሚል መሪ ሀሳብ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በዚህ አህጉራዊ መድረክ ላይ ሚኒስትሮች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች፣ የፓርላማ አባላት፣ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ወጣቶችና ሴቶች፣ የልማት አጋሮች ተወካዮችና ዲፕሎማቶች እየተሳተፉ ነው፡፡

በጉባኤው የዛሬ ውሎ የአፍሪካ የሴቶች የፖለቲካ አመራር ጉባኤና የወጣቶች የፖለቲካ መድረክ ይካሄዳል፡፡

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

በመሳፍንት ብርሌ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.