ለአየር ንብረት ለውጥ የተባበረ ፈጣን ምላሽ መስጠት ያስፈልጋል – አንቶኒዮ ጉቴሬዝ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ለአየር ንብረት ለውጥ የተባበረ ፈጣን ምላሽ መስጠት ያስፈልጋል አሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፡፡
ዋና ጸሃፊው በቱርክ አንታሊያ እየተካሄደ በሚገኘው የኮፕ 31 የመሪዎች ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የካርበን ልቀት እና የሙቀት መጠን መጨመር እንዲሁም በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እየተባባሱ የመጡ አደጋዎች ዓለምን እየፈተኗት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳት ከሀገራት የምላሽ ዝግጅት ጋር እንደማይጣጣም ገልጸው፤ ሀገራት ለአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ ያሳዩት መዘናጋት ዓለምን ለአደጋ እያጋለጣት ነው ብለዋል፡፡
ጥናቶች እጅ እንድንሰጥ ሳይሆን እንድንታገል ነው የሚነግሩን ያሉ ሲሆን፤ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ሀገራት የገቡትን ስምምነት እንዲያከብሩ እና አዳዲስ የፖሊሲ አማራጮችን መተግበር እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በተለይም የቅሪተ አካል ነዳጆች በአየር ንብረት ላይ ከፍተና ጉዳት እያደረሱ መሆኑን ጠቁመው፤ መንግሥታት በቅሪት አካል ነዳጅ ኩባንያዎች ላይ ከፍተኛ ግብር እንዲጣል ጠይቀዋል፡፡
የቅሪት አካል ነዳጅ መጥፋት እንዳለበት ጠቁመው፤ መንግሥታት በነዳጅ እና ጋዝ ምርቶቻቸው ላይ ገደብ ሊያደርጉ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
#ኢትዮጵያ #ኮፕ_32_ኢትዮጵያ #COP31 #COP32 #COP32ETHIOPIA
#fanamediacorporation
በሚኪያስ አየለ