ኢትዮጵያ የጎረቤት ተጠቃሚነት የሚገዳት ሀገር
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ለጎረቤት ሀገራት ቅድሚያ የሚሰጥ ነው፡፡ ምክንያቱም የኢትዮጵያን ሰላም፣ ደኅንነት እና ብልጽግና ከምሥራቅ አፍሪካ ቀጠና መረጋጋትና የጋራ ተጠቃሚነት ጋር በቀጥታ የተገናኘ በመሆኑ ነው።
የሀገራቱን የልማት እና ሰላም ጉዳዮችን ኢትዮጵያ እንደ ራሷ ጉዳይ አድርጋ በልዩ ትኩረት የምትሰራበት ነው፡፡ ይህ እውን እንዲሆን ኢትዮጵያ በተግባር የተደገፉ ሥራዎችን እያከናወነች መጥታለች፣ እያከናወነች ትገኛለች፣ ወደፊትም አጠናክራ ትቀጥላለች።
ለአብነትም በ2011 ዓ.ም ሱዳን ከፍተኛ ቀውስ ሲገጥማት ቀድማ የማሸማገል ጥረት ያደረገችው ኢትዮጵያ ናት፡፡
አሁን በቅርቡም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሱዳን ቡድኖች ችግሮቻቸውን ያለማንም ጣልቃ ገብነት እንዲፈቱ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፤ ይህ እንዲሳካ ኢትዮጵያ አስፈላጊው ሁኔታዎችን እንደምታመቻች አረጋግጠዋል፡፡
የሀገር መከላከያ ሰራዊት በቀጣናው ሀገራት፣ በአፍሪካ ህብረትና በተባበሩት መንግሥታት የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች በተደጋጋሚ ተሰማርቶ ግዳጁን በከፍተኛ ሙያዊ ብቃት ተወጥቷል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመከላከያ ሰራዊት አቅምን ማጠናከር በቀላሉ ሰላሙ የሚናጋ ቀጣና ችግር ሲገጥመው ወንድሞቻችንን ለማገዝ በሚያስችል ደረጃ ዝግጅት እያደረገ ያለ ተቋም ነው ይላሉ።
ማንንም የማጥቃት ፍላጎት የለንም በማለት ገልጸው፤ ኢትዮጵያ ለአካባቢ ሰላም መከበር ራሷን የምትቆጥረው እንደ ታላቅ ወንድም ነው ሲሉ ያስገነዝባሉ።
ይሄ ደግሞ አባባል ሳይሆን በኮሪያ፣ በዴሞክራቲክ የፐብሊክ ኮንጎ፣ በሩዋንዳ፣ በቡሩንዲ፣ በላይቤሪያ፣ በሱዳን፣ በሶማሊያ ተሰልፈን ሞተን ያሳየነው የሚታወቅ ተግባራችን ነው በማለት ያስታውሳሉ።
ዓባይን በፍትሃዊነት መጠቀምን በተመለከተም ግብጽ እና ሱዳን የሚበቃቸውን ውሃ እንዲያገኙ ኢትዮጵያ በኃላፊነት ስሜት እየሰራች መሆኑን ይናገራሉ፡፡
ዓባይ የኛ ብቻ ሳይሆን ለጎረቤቶቻችንም ሀቃቸው ስለሆነ እናከብራለን፣ እንጠብቅላቸዋለን ሲሉ አብራርተዋል፡፡
ኢትዮጵያ ብቻዋን የመልማት፣ የማደግ ፍላጎትም መርህም የሌላት ሀገር መሆኗን አጽንኦት ሰጥተው፤ ለዚህ ማስረጃው ደግሞ ኢትዮጵያ ለሁሉም ጎረቤት ሀገራት ንጹህ ውሃ እየሰጠች መሆኗን ተናግረዋል፡፡
ለኤርትራ፣ ለሶማሊያ፣ ለደቡብ ሱዳን፣ ለኬንያ፣ ለሱዳን ወንዝ እንዲሁም ለጅቡቲ ቱቦ ዘርግታ ውሃ እየሰጠች መሆኗን አንስተዋል፡፡
ብቻችን የመጠቀም ፍላጎት የለንም፤ በህግና ስርዓት የሚጠቀሙትንም እናግዛለን፣ እንተባበራለን፣ የጎረቤት ሀቅ መጠበቅ አለበት ብለን በደንብ እናምናለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከአብራኳ የሚፈልቀውን ውሃ ለሁሉም ጎረቤቶቿ እያጋራች በጋራ ለመልማትና ለማደግ ጥረት ብታደርግም፤ አንዳንድ ሀገራት ግን ኢትዮጵያ የባህር በር እንዲኖራት ስትጠይቅ እንደ ስህተት ይቆሩታል ሲሉ የሀገራቱን የአመክንዮ በጣረስ ብራርተዋል፡፡
ኢትዮጵያ ለቀጣናው ብሎም ድንበር ለምትጋራቸው ሀገራት ሰላም እና ልማት መሳካት በምታደርገው አስተዋፅኦ ልክ የቀጣናው ሀገራት ለጥያቄዎቿ ምላሽ ማግኘት ሊደግፏት ይገባል፡፡
ምክንያቱም ባለ ግዙፍ ኢኮኖሚዋ ሁለተኛዋ ትልቅ የህዝብ ቁጥር ያላት ኢትዮጵያ ማደግ፣ ለቀጣናው ማደግ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡
በቴዎድሮስ ሳህለ