Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል የከተሞችን የመጠጥ ውሃ ሽፋን 40 በመቶ ለማድረስ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በቀጣዮቹ ስድስት ወራት የትግራይ ክልል ከተሞችን የመጠጥ ውሃ ሽፋን 40 በመቶ ለማድረስ በትኩረት እየተሰራ ነው አለ የክልሉ ባለአደራ አስተዳደር፡፡

በባለአደራ አስተዳደሩ የመጠጥ ውሃ እና ሳኒቴሽን አቅርቦት ዳይሬክቶሬት የቀጣዮቹን ስድስት ወራት የሥራ ዕቅድ አጽድቋል።

በዚህም የውሃ ተደራሽነትን በማጠናከር የከተሞችን የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋን ወደ 40 በመቶ ለማድረስ መታቀዱ ተመላክቷል፡፡

በተመሳሳይ የክልሉን የገጠር የመጠጥ ውኃ ተደራሽነት ሽፋን ወደ 45 በመቶ ለማድረስ እንደሚሰራ ነው የተገለጸው፡፡

በሌላ በኩል የማይሰሩ የውሃ ተቋማትን መጠን ወደ 25 በመቶ እና የከተሞችን የውሃ ብክነት ወደ 20 በመቶ ዝቅ ለማድረግ መታቀዱ ተጠቁሟል፡፡

በድርቅ ወቅት የሚከሰተውን የውሃ እጥረት ለማቃለል ፈጣን እና ዘላቂ መፍትሄዎችን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቅሷል፡፡

ዕቅዱን በስኬት ለማከናወንም መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ አጋር አካላት በቅንጅትና በትብብር እንዲሰሩ ጥሪ ቀርቧል፡፡

በአሸናፊ ሽብሩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.