Fana: At a Speed of Life!

ኮቪድ-19ን ለመከላከል የተሰሩ ሥራዎችን የሚያሳይ አውደርዕይ ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10 ፣ 2013(ኤፍ.ቢ.ሲ) ኮቪድ- 19ን ለመከላከል በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተሰሩ ስራዎችን የሚያሳይ አውደርዕይ በጅማ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢ ተከፍቷል።

አውደርዕዩን የከፈቱት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ እና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቴክኖሎጂና የሰው ሃብት ልማት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ እምዬ ቢተው መሆናቸው ተገልጿል።

አውደርዕይው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ2012 ዓ.ም ኮቪድ-19ን ለመከላከል እንዲውሉ ያከናወኗቸው አበይት ተግባራትና ውጤቶችን ለመገምገምና ልምድ ለመለዋወጥ ያለመ ነው ተብሏል።

በዚህ አውደርዕይ ላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በምርምር፣ በማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎትና በቴክኖሎጂ ሽግግር ያከናወኗቸውን አበይት ተግባራት ይዘው መቅረባቸው ተገልጿል።

በአውደርዕዩ 40 የሚጠጉ ዩኒቨርስቲዎች ተሳታፊዎች ሲሆኑ ለአንድ ሳምንት ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.