Fana: At a Speed of Life!

የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በዓል ለማክበር እየተደረገ ባለው ዝግጅት ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 15ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በዓል ለማክበር እየተደረገ ባለው ዝግጅት ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው።

ውይይቱ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አደም ፋራህ እና የክልል ምክር ቤት አፈጉባኤዎች በተገኙበት በቢሾፍቱ ነው እየተካሄደ ነው የሚገኘው።

በኮቪድ 19 ምክንያት የአከባበር ለውጥ የተደረገበት የዘንድሮው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል በተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎትና የህዝብ ለህዝብ ግንኙትና ትስስርን በሚያጠናከሩ መርሃ ግብሮች ሊከበር መታቀዱ ተገልጿል።

በዚህም በዓሉ በክልሎች የሚከበር ሲሆን በተናጠል እያደረጓቸው ያሉ ስራዎችንም አቅርበዋል።

ወቅታዊ ችግሮች ፈተና ቢሆኑም በዓሉ እርስ በእርስ ከመተዋወቅ ባለፈ የትስስር ተምሳሌት በመሆኑ በበቂ ዝግጅት ለማክበር እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውንም ገልፀዋል።

በሀብታሙ ተክለስላሴ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.