Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት 739 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ13 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትጵዮያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 6 ሺህ 985 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 739 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በዚህም በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 87 ሺህ 169 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓታት 823 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን÷ በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 40 ሺህ 988 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
እንዲሁም በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ የ13 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን አጠቃላይ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 325 ደርሷል።
በኢትዮጵያ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊየን 377 ሺህ 80 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.