Fana: At a Speed of Life!

437 ኢትዮጵያውያን ዜጎች ከሳዑዲ ዓረቢያ እና ከሊባኖስ ተመለሱ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 12 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 437 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ እና ከሊባኖስ መመለሳቸው ተገለጸ።

ከተመላሾች ውስጥ 293 የሚሆኑት ከጅዳ ከሳዑዲ ዓረቢያ የተመለሱ ናቸው ተብሏል፡፡

እንዲሁም 144 የሚሆኑት ደግሞ ከቤሩት ሊባኖስ የተመለሱ ናቸው።

ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች የተወከሉ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተው አቀባበል ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.