በኦሮሚያ ክልል 21 ሁለተኛ ደረጃ የትምህርት ቤቶች ግንባታቸው ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኑ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል 21 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታቸው ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸው ተገለፀ።
በክልሉ 11 ዞኖች በ2007 እና 2008 የበጀት ዓመት ተጀምረው ግንባታቸው በተለያዩ ምክንያቶች ሲጓተት የነበሩ 21 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ናቸው ተጠናቀው ነው ለአገልግሎት ዝግጁ የሆኑት።
እነዚህ ትምህርት ቤቶች እያንዳንዳቸው ከ750 እስከ 1 ሺህ ተማሪዎች ተቀብለው ማስተናገድ የሚችሉ መሆናቸውን በኦሮሚያ ክልል በምክትል ርእሰ መስተዳድር ማእረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ ገልፀዋል።
ግንባታቸዉ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ዝግጁ የሆኑ ትምህርት ቤቶችም፦
1. ኢሉአባቦር ዞን (ሲቦ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ዲዱ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት)
2. ምዕራብ ጉጂ ዞን (ቢዮ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ቶሬ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት)
3. ምስስራቅ ሀረርጌ ዞን (ዳዌ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት)
4. ምዕራብ ወለጋ ዞን (ሆማ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት)
5. ምስራቅ ሸዋ ዞን (ኬንታሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት)
6. አርሲ ዞን (ማጪቱ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት)
7. ምዕራቅ አርሲ ዞን (ቆሬ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት)
8. ምስራቅ ወለጋ ዞን (ገባ ከሚሳ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ሀሮ ሊሙ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት)
9. ጅማ ዞን (ኢልኬሁ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ሊሙ ሰቃ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ሼኪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት)
10. ባሌ ዞን (ቤልቱ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ጨልጨል ራይቱ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ቡሉቅ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣
አሊ ቢራ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት)
11. ሰሜን ሸዋ ዞን (ሳላይሽ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት) ናቸው።