Fana: At a Speed of Life!

የባህል አልባሳት የባለቤትነት እና የእደ ጥበብ ሀገር አቀፍ ማህበራት ምስረታ መድረክ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 26 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የባህል አልባሳት የባለቤትነት እና የእደ ጥበብ ሀገር አቀፍ ማህበራት ምስረታ መድረክ በአዳማ ከተማ ተካሂዷል።
በመድረኩ የተገኙት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው ÷መድረኩ ለዘመናት በሀገር ባህል አልባሳት ላይ የሚታዩ ዘመን አመጣሽ እና ቀደምት ችግሮችን ለመፍታት ትልቅ ሚና አለው ብለዋል።
ለዚህም ባለቤት የሆነው ህዝብ በህብረት በመሆን በዘርፉ ላይ የሚደርሰውን ችግር ለመፍታት አቅም የሚያገኝበትም ነው ሲሉ ተናግረዋል።
የባህል አልባሳት ከጥንት ጀምሮ ለህዝቡ በዕለት ተዕለት ተግባሩ ላይ የሚገለገልበት እና ለሀገር ኢኮኖሚ ከፍተኛ ፋይዳ ያለው በመሆኑ ይህንን በማሳደግና በዘርፉ የምናገኘው የውጭ ምንዛሬ ከፍ ለማድረግ እንዲሁም የባለቤትነት ጥያቄ መልስ የሚሰጥን ማህበር በመመሰረት ዘርፉን ከፍ ለማድረግ ይረዳልም ነው ያሉት።
ዶክተር ሂሩት አያይዘውም ይህንን ድንቅ የሆነውን የባህል አልባሳት ጥበብን ወደ ትውልድ ለማስተላለፍ እኛ ኢትዮጵያውያን ለዓለም ትልቅ እውቀት ማበርከታችንን በማሳመን ባህላችንን በማክበር ሀገራችን በዘርፉ የምታገኘውን ፋይዳ ከፍ እናደርጋለን ብለዋል።
በውይይት መድረኩ የባህል አልባሳት ምርቶች ዙሪያ እየታዩ ያሉ ችግሮች እና ለመፍትሄዎቻቸው የባለ ድርሻ አካላት ሚና እና የባህል አልባሳት በአዕምሮዊ ንብረት ለማስመዝገብ ያሉ የህግ ይዘቶች የሚሉ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት እንደተደረገባቸው ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.