በትግራይ ክልል ከ16 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው መድኃኒቶችና የሕክምና መገልገያዎች ተሰራጩ
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ለሚገኙ ጤና ተቋማትከ16 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው መድኃኒቶችና የሕክምና መገልገያዎች ተሰራጭተዋል።
ጤና ሚኒስቴር ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከ16 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የተለያዩ መድኃኒቶችና የሕክምና መገልገያዎች በትግራይ ክልል ለሚገኙ ለተለያዩ ጤና ተቋማት በኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ በኩል ማሰራጨቱን አስታውቋል።
መድኃኒቶቹና የሕክምና መገልገያዎቹ በመቀሌ፣ በአዲግራትና ሽሬ ከተሞች ለሚገኙ ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች ለእያንዳንዳቸው 3 በአጠቃላይ 9 መድኃኒት የጫኑ ተሸከርከሪዎችን በማጓጓዝ እንዲደርሳቸው ተደርገዋል።
ከተሰራጩ መድኃኒቶች መካከል መሰረታዊ ህይወት አድን መድኃኒቶችን ጨምሮ ለድንገተኛ፣ ለኩላሊት፣ ለደም ግፊት፣ ለስኳር ሕሙማን እንዲሁም ለእናቶችና ህጻናት ጤና አገልግሎት የሚውሉእንደሚገኙበት ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ከዚህ ቀደምም ለምዕራብና ደቡባዊ ትግራይ ዞኖች ዳንሻ፣ ሁመራ፣ ራያ፣ አላማጣ እና ሌሎች አካባቢዎች በአማራና አፋር ክልል የሚገኙ የኤጀንሲው 3 ቅርንጫፎች በኩል የሚያስፈልጉ መድኃኒቶች እና የህክምና ቁሳቁሶች እንደተሰራጩ ሚኒስቴሩ አስታውሷል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!